ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ኃላፊ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የተመራ የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን ከትናንት በስቲያ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዘንድሮውን ምርጫ ለሚታዘቡ 45 ሺህ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች ፍቃድ ሰጥቷል። ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ምርጫውን የሚታዘቡት በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ግብዣ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ለታዛቢዎች የመታዘብ ፈቃድ ይሰጣል።