ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫው ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ገለጸ!

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫው ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ገለጸ!

 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– 6ኛው አገራዊ ምርጫ፣ በሁሉም አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን የገለጹት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ አብዛኞቹ ምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ ጀምረው ምርጫውን እያከናወኑ መሆኑን አመልክተው፣ ይሁንና “በአዲስ አበባ ዘጠኝ ምርጫ ጣቢያዎች ሃላፊነት የጎደላቸው ምርጫ አስፈፃሚዎች በቦታው ሳይገኙ ቀርተዋል። ሆኖም ሌሎች 27 አስፈፃሚዎችን ቃለ መሃላ በማስፈፀም ስራ እንዲጀምሩ በመደረጉ የምርጫ ሂደቱ ዘግይቶ ተጀምሯል” ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል አምቦ አንድ የምርጫ ጣቢያ ምንም ሳይፈጠር የተደናገጡ ምርጫ አስፈፃሚዎች ቦታውን ለቀው መሸሻቸውንና የተፈጠረ ችግር ባለመኖሩ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እየተከናወነ መሆኑን አያይዘው የገለጹት የቦርድ ሰብሳቢዋ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና እጩዎችን ተሳትፎና ተዘዋውሮ የመታዘብ መብት መገደብ የተከለከለና በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY