ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ድረስ መራዘሙን የምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሶሊያና ሽመልስ አስታውቀዋል፡፡
“ለዚህም ምክንያቱ፤ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ዘግይቶ የተጀመረባቸው ቦታዎች በመኖራቸው፣ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ የቁሳቁስ ስርጭት የዘገየባቸው ቦታዎች በመኖራቸው፣ ድምፅ ለመስጠት ረጅም ሰልፎች ላይ ያሉ ዜጎች በመኖራቸው ነው” ነው ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ፣ በዚህም መሰረት የምርጫ አስፈፃሚዎች እስከ 3 ሰዓት ድረስ የሚመጣ ማንኛውንም መራጭ እንዲያስተናግዱ ቦርዱ ጥሪ መተላለፉን አመልክተው “ሆኖም መራጮች መርጠው ያጠናቀቁባቸው እና ለመምረጥ የተሰለፉ ዜጎች በተጠናቀቁበት ቦታዎች የምርጫ ጣቢያውን መዝጋት እና የቆጠራ ሥራ መጀመር ይችላሉ” ብለዋል።