“ራዲሰን ብሉ ሆቴል” ውስጥ ሞተው የተገኙት አሜሪካዊ  ታዛቢ አለመሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ!

“ራዲሰን ብሉ ሆቴል” ውስጥ ሞተው የተገኙት አሜሪካዊ  ታዛቢ አለመሆናቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ!

ኢትዮጵያ ነገ ዜናዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ሟቹ ኪስ ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልዩ የምርጫ ታዛቢ ወረቀት (ባጅ) እና ሌሎች ቁሳቁሶችን አግኝቻለሁ ሲል መናገሩ ይታወሳል።

ይሁንና፣ ከደቂቃዎች በፊት ወቅታዊ መግለጫ የሰጡት የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ፣ ግለሰቡ የካርተር ሴንተር አለም አቀፍ ታዛቢ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።

ግለሰቡ እንደማንኛውም ድጋፍ ሰጪ አለም አቀፍ ተቋም በታዛቢነት ሳይሆን በእንግድነት ከቦርዱ ባጅ መውሰዳቸውንና ግለሰቡ የተሰጣቸው “የልዩ የእንግድነት ባጅ” መሆኑን የገለጹት ሶሊያና “በዚህ የልዩ ባጅ የምርጫ ሂደቱን የመከታተል ነገር ግን የመታዘብ ስራ ለማይሰሩ አጋር ድርጅቶች የሚሰጥ ባጅ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

“ከካርተር ሴንተር ምርጫውን ለመታዘብ የመጣ ታዛቢ የለም” ያሉት ወ/ሪት ሶሊያና “አሟሟታቸውን ቦርዱ ሰምቷል በዚህም አዝኗል ፤ አማሟታቸው በመንግስት ፖሊስ እና በሌሎች ተቋማት እየታየ እንደሆነ ሰምተናል። ነገር ግን ከምርጫው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም” ሲሉም ተናግረዋል።

 

LEAVE A REPLY