ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎቹን ፍላጎት ለማሟላት የሚያካሄደውን ሁለገብ ጥረት እንደምትደግፍ ነው ካናዳ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ያስታወቀችው።
የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ጋርኒው እና የአገሪቱ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ካርማ ጎልድ በጋራ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የወሰደውን የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ ካናዳ እንደምትቀበለው አስታውቀዋል።
ከየትኛውም ወገን ይሁን በትግራይ ክልል በነበረው ቀውስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ ወሳኝ መሆኑንም አሳስባለች።
ሁሉም ወገኞች ይህንን የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ እድል በመጠቀም ለግጭቶች ሰላማዊ መፍትሄ ለመሻት እንዲጠቀሙበትና በቀጠናው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን አበርክቶ እንዲያደርጉም ነው ጥሪ ያቀረበችው።