ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የህወሓት ታጠቂዎች በኮምቦልቻ ከተማ ከ100 በላይ ወጣቶችን መጨፍጨፉን መንግስት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ዛሬ እንዳስታወቀው የጁንታው ሀይል ጥቅምት 21/02/14 ዓ.ም ሌሊት በኮምቦልቻ ከተማ ሰርጎ በመግባት ከ100 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ማድረጉን እና በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን ዶ/ር ለገሰ ቱሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትሩ ዛሬ ይፋ አድርገዋል።