ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሚንስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴዎን ጢሞቴዎስ ገለፁ፡፡
6 ወር የሚቆየው ይህ አዋጅ እነዚህን እና ሌሎችንም ያካትታል። እድሜአቸው የደረሰበ ሙሉ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ ትጥቅ ኖሯቸው መዝመት የማይችሉ ትጥቃቸውን ለሌላው ማስረከብ እንዲችሉ ያደርጋል።
ማንኛውንም የሰው ቤት እና የህንፃ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መበርበሪያ (መፈተሽ) እንዲችል ማድረግ ይችላል።
የሰአት እላፊ በማንኛውም ቦታ ማድረግ ይችላል
ህዝቦች ለተወሰነ ጊዜ አንድ ቦታ እንዲቀመጡ ማድረግ ይችላል። ማንኛውንም የመገናኛ ዘዴዎችን እና የመጓጓዧ ዘዴዎችን መዝጋት ይችላል፤ መንገዶችን አገልግሎት መስጫ መስሪያ ቤቶችን መዝጋት ይችላል።
አዋጁ በ48 ሰአት ውስጥ ይፀድቃል ተግባራዊነቱ ከዛሬ ጀምሮ ይጀምራል ተብሏል።