መፍትሄው በእጃችን ነው || ላቀ አያሌው

መፍትሄው በእጃችን ነው || ላቀ አያሌው

አሸባሪው የትግራይ ወራሪና ዘራፊ ኃይል በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ አማራን ማኅበራዊ እረፍት በመንሳት እንዲሁም አገር አልባ ባለአገር በማድረግና በቀንደኛ ጠላትነት በመፈረጅ ኮሽ ባለ ቁጥር ሲያሳድደው፣ ሲያስረው፣ ሲገርፈው፣ በየማጎሪያ ጣቢያው ሰቆቃ ሲፈጽመበት ብሎም አድኖ ሲገድለው እንደቆየ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሕያው ምስክር ነው ፡፡ ትሕነግ አማራን እንደ ሕዝብ አዋርዶ፣ አደህይቶና ገባሪ አድርጎ እንዲሁም ሥነ-ልቦናውን ሰብሮ ከፍ ሲልም ማንነቱን አጥፍቶ ሁሉንም ሐብትና ንብረቱን በዘረፋ ወደ ትግራይ አጓጉዞ ራሱን የማበልፀግ ሕልሙን ለማሳካት በሌላ ዙር ምዝበራ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም አሸባሪው የትግራይ ወራሪና ዘራፊ ኃይል በፖለቲካ የመድረክ ትግል በሽንፈት ያጣውን የጠቅላይነት ሥልጣን መልሶ በብረትነካሽነት ለማስመለስና ከጦር አውድማ ለማግኘት አገራችንን በክህደት ከጀርባ መውጋቱ አልበቃው ብሎ ከሐምሌ 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአማራና በአፋር ክልሎች የእብሪት ወረራ በመፈፀም በአማራና በአፋር ሕዝቦች ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው የዘር ፍጅት፣ አረመኔያዊ የሆነ ግድያና ሰቆቃ እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን እምነትና እሴት ውጭ በሆነ መንገድ እንስሳዊ ባህሪ የተገለጠበት በቡድን አስገድዶ የመድፈር፣ የእምነት አባቶችን በቤተመቅደስና በመስጊድ የማረድ ወንጀሎችን ፈፅሟል፤ እየፈፀመም ይገኛል:: ስለሆነም ወሎ: ሸዋ: ጎንደርና ጎጃም ሁሉም የክልላችንን ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያን ጋር ተቀናጅተን በአሸባሪው የትግራይ ወራሪና ዘራፊ ቡድን ወረራ ሥር ያሉ የአማራ ሕዝብ መኖሪያ አፅመርስቶችን ነጻ ማውጣትና ወራሪውን ኃይል እስከ ወዲያኛው በመደምሰስ የተዋረደውን የሕዝባችንን ክብር ማስመለስና ኢትዮጵያን ከመፍረስ መታደግ ይኖርብናል :: ይህን ተግባር ለመፈፀም ሁላችንም አፍከልብ በሆነ መንገድ መንቀሳቀስ አለብን::

የትግራይ ወራሪ ሀይል በለመደውቅጥፈቱ  እያናጠለ ለመጨረስ እንዲመቸው የእኔ ጠላት እነእከሌ ናቸው እያለ ማደናገሩን ተያይዞታል:: በሌላም በኩል ሰርጎገብ ወያኔዎችና የእኛው የውስጥ ባንዳዎች አሉቧልታና ወሪ በመልቀቅ እያሸበሩ ይገኛሉ:: በወሪና በአሉቧልታ ሳንበገር የደፈረንን ወራሪ ሀይል ለመደምሰስ መፍትሄው በእጃችን ነው:: ባለስልጣንም ሆነ ባለሀብት ከህዝባችን ጋር ሁላችንም ጠላትን መፋለም አለብን።

LEAVE A REPLY