ለህወሓት ድጋፍ ሊውል የነበረ 37 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተያዘ

ለህወሓት ድጋፍ ሊውል የነበረ 37 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተያዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ለአሸባሪው ህወሓት ድጋፍ ሊውል የነበረ 37 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ በርካታ ገንዘብና የጦር መሳሪያዎች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ እና ገንዘቡ የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ወንድይራድ ትምህርት ቤት አካባቢ ፖሊስ ሕብረተሰቡ የሰጠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ባከናወነው ፍተሻ ነው ተብሏል፡፡
የኮተቤ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ኮማንደር በየነ ዱሬሳ÷ ህብረተሰቡ የሰጠውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ ግለሰቡ በብርበራ እንዳይገኝበት በማሰብ 37 ሺሕ የአሜሪካ ዶላር፣ 52 ሺሕ ብር እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችን በፌስታል ጠቅልሎ ግቢው ውስጥ ደብቆ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

LEAVE A REPLY