ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቅንጅት የፈጠሩት አካላት በተባበረ ክንዳችን ይፈርሳሉ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷ዛሬ እንኳን ህዝቡ ምድሩ ሳይቀር ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እየተዋጋ ባለበት የጀግኖች መገኛ ምድር አፋር ተገኝተናል ብለዋል፡፡
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና የኢትዮጵያ ከብረት የጠነከረ ምሽግ፣ እንኳን ሕዝቡ ግመሎቹ እንኳን በኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደሩት፣በታሪኩ የባንዳነት ሳይሆን የጀግንነት የሆነው የአፋር ህዝብ ኢትዮጵያን አደጋ ላይ ሊጥል የመጣ የትኛውም ወራሪ በአፋር ምድር ትቢያ ሆኖ እንዲቀር እያደረገ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
አሸባሪዉ ጁንታ የእናት ጡት ነካሽ ያሰበው ሁሉ አልሳካ ሲለው ህፃናትን፣ ሴቶችና አቅመ ደካሞችን በተኙበት በከባድ መሳሪያ ሳይቀር በመደብደብ የፈሪ በትሩንና ፋሽስታዊ ግፉን መፈጸሙንም አንስተዋል፡፡
አሁን ላይም ጀግናው የመከላከያ ሰራዊትና የአፋር ልዩ ሃይሎች እየተከታተሉ የእጁን እየሰጡት ይገኛሉ ሲሉም ተናግረዋል።