ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በቤልጅየም በብራስልስ የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ እየተካሄደ ነው ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ያልተገባ ጫና የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በቤልጂየም መዲና ብራሰልስ እየተካሄደ ነው።
በአውሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት እየተካሄደ ባለው ሰልፍ ላይ ቤልጂየም፣ ጣልያንና ኔዘርላንድን ጨምሮ በስምንት አውሮፓ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ሰልፈኞቹ ‘ምዕራባውያን አገራት ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ የሚያሰራጩትን የሐሰት መረጃ ያቁሙ፣ እኛ ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያውያን ጎን ነን” የሚሉ መልዕክቶችን በማንጸባረቅ ላይ ናቸው።