የኢትዮጵያን ችግር በውጪ ጣልቃ ገብነት መፍታት እንደማይቻል የአሜሪካ የቀድሞ አምባሳደሮች አሳሰቡ

የኢትዮጵያን ችግር በውጪ ጣልቃ ገብነት መፍታት እንደማይቻል የአሜሪካ የቀድሞ አምባሳደሮች አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ችግር በውጪ ሀገራት ጣልቃ ገብነት ሊፈታ እንደማይችል እና መፍትሄው ከውስጥ መምጣት እንዳለበት የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ አምባሳደሮች አምባሳደር ቲቦር ናዥ እና አምባሳደር ዶናልድ ቡት ተናግረዋል።

አምባሳደሮቹ የዘር መከፋፈል ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ችግር እንደዳረጋት ገልፀው ኢትዮጵያውያን ልዩነታቸውን አቻችለው በአንድነትና በሰላም መኖር የሚችሉበትን መንገድ መፈለግ አለባቸው ብለዋል።

በኢትዮጵያና በጊኒ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉትና በትራምፕ አስተዳደር ረዳት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ቲቦር ናዥ እንዲሁም በኢትዮጵያ፣ ላይቤሪያ እና ዛምቢያ አምባሳደር የነበሩት ዶናልድ ቡት ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያውያን ለውጪ ኃይል ግፊት የማይንበረከኩ መሆናቸውን ማስተዋላቸውንና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሚና ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንዲፈቱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY