ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትምህርቱ ዘርፍ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት ማሳደግ እንደሚገባ ገለጹ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትምህርቱ ዘርፍ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት ማሳደግ እንደሚገባ ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና የዩኔስኮ ዋና ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ ባዘጋጁት የዓለም አቀፉ የትምህርት ስብሰባ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ፕሬዚዳንቷ በበይነ መረብ አማካኝነት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንዳነሱት ÷ በትምህርት ዘርፉ ላይ ተጨማሪ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም ፕሬዚዳንቷ እንደ ዓለም አቀፍ የትምህርት ኮሚሽን ሰብሳቢነታቸው በወደፊቱ የትምህርት ዘርፍ የመላው ሴቶችን በተለይም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ሰለባ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ተጠቃሚነት አኳያ ጥረት እንደሚያደርጉም ነው የገለጹት።

LEAVE A REPLY