ፖለቲከኛው አቶ ዘለቀ ረዲ ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደብዳቤ ላኩ

ፖለቲከኛው አቶ ዘለቀ ረዲ ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደብዳቤ ላኩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ላይ እያራመዱ የሚገኙትን ፖሊሲ ደግመው እንዲፈትሹ በዚህም ከኢትዮጵያና ከያዘችው እውነት ጎን እንዲቆሙ የኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና መኃንዲስ ዘለቀ ረዲ ለባይደን በጻፉት ደብዳቤ ጠየቁ።

ፖለቲከኛና መኃንዲሱ ለፕሬዝዳንቱና አዲስ አበባ ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በኢሜይል በላኩት ደብዳቤ “ኢትዮጵያዊያን አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ አገራችንን እንታደጋታለን፤ ኢትዮጵያ የመን አሊያም ሶሪያ አይደለችም” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያና አሜሪካ በመሪዎች መለዋወጥ ያልተቋረጠና ዘመናትን የተሻገረ መልካም ግንኙነት እንዳላቸው ጸሐፊው አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ በማንኛውም አገር ላይ ወረራ ፈጽማ የማታውቅ ብትሆንም ግልጽ ባለሆነ ምክንያት ግን ወረራረዎች ይፈጸሙባታል ሲሉም አክለዋል፡፡

LEAVE A REPLY