ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገሪቱ ያለውን እውነታ በማሳየትና የውጭ ጫናን በመቃወም ውጤታማ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡
ቃል አቀባዩ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ከቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የኬኒያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ማድረጋቸው ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከካናዳ እና ከስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ እና በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ በስልክ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ረገድ በሳምንቱ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵዊያንን ወደ አገር መመለስ ተችሏል ብለዋል።