በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ...

በደብረ ብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ26 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘውንና አጠቃላይ ግምቱ ከ26 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ የአልባሳትና የምግብ ቁሳቁስ በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ሕወሓት በዜጎች ላይ ዘርፈ ብዙ ቀውሶች እያስከተለ መሆኑን ተናግረው ወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ተረዳድቶ ማለፍ ያለበት ጊዜ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የተደረገው ድጋፍም በተለይ በጉምሩክ ኮሚሽን ማህበራዊ ሃላፊነትን ከመወጣት አኳያ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ በመሆኑ በሚኒስቴሩ ስም አመስግነዋል፡፡

LEAVE A REPLY