ኮንጎ በኢትዮጵያ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚደረግን ጥረት እንደምታወግዝ አስታወቀች

ኮንጎ በኢትዮጵያ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚደረግን ጥረት እንደምታወግዝ አስታወቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜናበኢትዮጵያ ስልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚደረግን ጥረት እናወግዛለን ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቴሺኬዲ ለአቶ ደመቀ መኮንን መልእክት ልከዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፍ ሉቱንዱላ ጋር ተወያይተዋል የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፌሊክስ ቴሺኬዲ የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርበት ሲከታተሉ መቆየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፍ ሉቱንዱላ ለአቶ ደመቀ ገልጸዋል።

በውይይታቸው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሚስተዋለውን ግጭት ለመፍታት ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የአፍሪካ ህብረት ሊኖራቸው በሚችለው ሚና ዙሪያ መክረዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን፤ የኮንጎ ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያ የተጀመረውን የሰላም ጥረት ለመደገፍና ለማበረታታት ያደረጉትን ተነሳሽነት ማድነቃቸው ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ፕሬዝዳንት ቴሽኬዲ አጋርነትንና ወንድማማችነትን ለማሳየት፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሰላም መምጣት ያላቸውን ቁርጠኝነትን ለማሳየት ከፍተኛ የባለስልጣናት ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል ተብሏል።

LEAVE A REPLY