በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምዕራባውያን የሚያደርጉትን ጣልቃገብነት ተቃወሙ 

በእንግሊዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምዕራባውያን የሚያደርጉትን ጣልቃገብነት ተቃወሙ 

ኢትዮጵያ ነገ ዜናሰልፈኞቹ የእንግሊዝ መንግሥት በኢትዮጵያውያን የተመረጠው መንግሥት ላይ ጫና ከማድረግ እንዲቆጠብ እና እንግሊዝም ሆነች አሜሪካ ከኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ጠይቀዋል።

“ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫችን ነው፤ ሕዝባችንን ለዘመናት ሲያሰቃይ የቆየውን አሸባሪውን ህወሓት ‘ፈፅሞ አይሆንም’ እንለዋለን፤ የአፋር እና የአማራ ሕዝብ በሽብር ቡድኑ መሞት ይብቃ” የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮችንም አሰምተዋል።

በተመሳሳይ ዜና የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በእስራኤል ተካሄዷል።

በእስራኤል የሚኖሩ ትውልድ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት ጫና እንዲያቆሙ፣ እስራኤል ለኢትዮጵያ መንግስት የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል ጥያቄ ማቅረባቸውን ከእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

LEAVE A REPLY