‘’በግንባር መሰለፍን ጨምሮ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ’’ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ገለፁ

‘’በግንባር መሰለፍን ጨምሮ የሚጠበቅብኝን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ’’ ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ በኢትዮጵያ የተደቀነው አደጋ አፍሪካን የማንበርከክ ዓላማ ጭምር ያነገበ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ሙከራ መሆኑን ገልጿል።

ኢትዮጵያ የጥቁር ሕዝቦች የነጻነት ምልክት መሆኗን የገለጸው ኃይሌ፤ ኢትዮጵያን በማንበርከክ የጥቁር ሕዝቦችን አኩሪ ታሪክ ለመቀማት የተቀናጀ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ ክብር ወደ ግንባር መዝመታቸው አገሩን ከሚወድ መሪ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የእርሳቸውን ፈለግ እንዲከተል ጥሪ አቅርቧል።
መላ አፍሪካዊያን ትግሉ የሁሉም ጥቁር ሕዝቦች መሆኑን በመገንዘብ ከኢትዮጵያ ጎን እንዲቆሙም ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም ኢትዮጵያዊያን በግንባር ከመዝመት ባሻገር በደጀንነትም በንቃት መሳተፍ እንደሚጠበቅባቸውም አትሌት ኃይሌ አስገንዝቧል።

በመጨረሻም አትሌቱ የዕለት ተዕለት ተግባራችን አሸባሪው ህወሓት ያወደመውን ሃብትና ለወደፊት ለመልማት ያለንን ውጥን ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበትም ገልጿል።

LEAVE A REPLY