አሜሪካና መሰሎቿ ጠብቀን ያቆየነውን ሉዓላዊነታችንን ያክብሩልን ሲሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ

አሜሪካና መሰሎቿ ጠብቀን ያቆየነውን ሉዓላዊነታችንን ያክብሩልን ሲሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ፖለቲከኛው ፕሮፌሰር በየነ እንደገለጹት፤ አሜሪካንን ጨምሮ አንዳንድ የምዕራባውያን አገራት ኢትዮጵያን የማፍረስና ሽብርተኛ ቡድንን የመደገፍ እንቅስቃሴያቸውን ትተው ለዘመናት ጠብቀን ያቆየነውን ሉዓላዊነታችንን ያክብሩልን።

አሜሪካም ሆነ መሰሎቿ በተለያዩ መንገዶች ሽብርተኛውን የሕወሓት ቡድን የመደገፍ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ አመልክተው፤ እነዚህ አገራት በዕርዳታ ስም የሚወረውሩልን ጥቃቅን ትርፍራፊያቸውን ወስደው ሉዓላዊነታችን ያክብሩልን ብለዋል።

አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት በተለይ ደግሞ አሜሪካ ወንጀለኛና ሽብርተኛ ብለው ከፈረጁት ቡድን ጋር ለድርድር የማይቀመጡና ይልቁንም የተለያዩ አገራትን እንኳን እኛ ሽብርተኛ ብለን ከፈረጅነው ድርጅት ጋር ተገናኝታችኋል በሚል ማዕቀብ የሚጥሉ አገራት መሆናቸውን አንስተዋል።

LEAVE A REPLY