የጦርነትን አስከፊነት በስራ አጋጣሚ የተለያዩ አፍሪካ አገራት የጦርነት ጠባሳ አይቸ አገሬ ኢትዮጵያ ጦርነት እንዳይኖር ስመኝ ነበር ሆኖም ግን እንዳለመታደል ሆኖ እማማ ኢትዮጵያ ላለፋት 13 ወራት ጦርነት ውስጥ ናት!
የጦርነት አሰከፊነት በደንብ የሚገባችሁ በራሳችሁ፣ በቤተሰባችሁ፣ በጓደኞቻችሁ ፣በምታውቋቸው ወይም በምታውቁት አካባቢ ሲደርስ ነው! እኔንም ያጋጠኝ ይህ ነው!
ወልዲያ ተያዘ ሲባል ደነገጥኩ ፣ ውጫሌ ሲያዝ እጅግ ተስፋ ቆረጥኩ (ወደፊት ሊሆን የሚችለውን በማሰብ)፣ ታላቋ ደሴና ኮምቦልቻ ሲያዙ አነባሁ፣ አለቀስኩ!!!
ጉጉፍቱ ፣ጊምባ (ቱሉአውሊያ)፣ አቀስታ፣ ወይን አምባ፣ ልጓማ፣ ወረኢሉ ፣ጃማ እና ሌሎች ቦታወች የተፈጠረውን ስሰማ እጅግ አዘንኩ!!!
ትላንትና የትውልድ ቀየ ከላላ(ቲርቲራ ናገቢሳ ) በተፈጠረው ግን ልቤ ደማ! የልጅነት ትውስታየን ቀማኝ !!! እትብቴ የተቀበረበት መንደር ገቢሳ የጦር አውድማ ሆኖ ዋለ! ለመጀመሪያ ጊዜ ፊደል የቆጠርኩበት የቲርቲራ ትምሀርት ቤቴ ግቢ የተኩስ ድምፅ ሲያስተጋባ ዋለ!
የተወለድኩበት ቤት ፊትለፊት ያለውና ልጅ ሆኘ ከእንቅልፌ ሰነሳ ሁል ጊዜ የማየው ተራራ እና ተራራ ማለት ምን እነደሆነ ያወኩበት ከዛም በጎችና ፍየሎች የጠበኩበት ፣ መፅሐፍትና ቁርዓርን ቁጭ ብየ ያነበብኩት ፣ ክረምት ላይ ጅራፍ ያኖጋሁበት ፣ የቀጋና አጋም ፍሬ የበላሁበት የጎሮዝጊሃር ተራራ የወገን የጦር ምሽግ ሆኗል አሉኝ!! ከመንደራችን ጀርባ ያለዉ ሌላ ተራራ ደግሞ የጠላት ጦር ምሽግ ነው!! ልበበሉ እኔ የተወለድኩበት መንደር በሁለት ምሽጎች መሀል ነው የለው!!
እናቶች ህፃናትንና እንሰሳት ይዘው ወደ አጎራባች ቀበሌዎች በቀት ሄደዋል( ተፈናቅለዋል )!
ትናንት አጎቶቸናሌሎች ዘመዶቸ ከከላላ ወረዳ ከተውጣጡ ሚሊሻወች እንድሁም አካባቢውን ለመርዳት ከመጣው ጀግናው የጎንደር አርማጨሆ ፋኖ ጋር ሆነዉ በጀግንነት እየተፋለሙ ነበር ! አዳራቸው እንዴት እንደሆነ እናም ዛሬ ጧት ስላለው ሁኔታ ስልክ ስለማይሰራ ማወቅ አልቻልኩም።
ጀግኖቹ ወራሪውን ኃይል ቀጥቅጠው እንደሚያባርሩት ተስፋ አደርጋለሁ! ሆኖም ግን ጠላት ተሳክቶለት ከላላ ከተማን ከተቆጣጠረ የ85 ዕድሜ ባለፀጋ ወላጅ እናቴ እና ሌሎች ቤተሰቦቸ፣ ዘመዶቸ ፣ አብሮ አደጎቸ ፣ኮትኩቶ ያሳደገኝ ህዝብ እንድሁም የዛሬው ማንነቴ የተገነባባት ከላላየ ምን ይሆኑ ይሆን ?!!
ወገኖቸ ጦርነት እጅግ በጣም አስከፊ ነው!!! አላህ በቃ ይበለን!!!