ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአሁን ወቅት ሱዳን በወረራ የያዘቻቸውን ስፍራዎች በሰላማዊ መንገድ እንድትለቅ እና በአሸባሪነት የተፈረጀው ቡድን ሱዳን ድንበር እንዳይሸሸግ እየተሰራ እንደሚገኝ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰለማዊት ካሳ አሳወቁ።
ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የሱዳን ወታደሮች ላይ ጥቃት ስለመሰንዘሩ የተሰራጨው መረጃ ከእውነታው የራቀ ነው” ያሉት ሚንስትሯ እርምጃ የተወሰደው በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት ለማድረስ በመጣ አካል ላይ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተላለፉትን ክልከላዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሚተላለፉ እና ሐሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ አሳስበዋል።