ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባለፉት አራት ወራት ተግባራዊ የነበረውን የብድር ክልከላ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን አስታወቀ።
በመሆኑም ብሔራዊ ባንክ ሁሉም ባንኮች ለሁሉም ደንበኞቻቸው የብድር አገልግሎት እንዲሰጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ይፋ አድርጓል።
የብድር ክልከላው የተጣለው የኢኮኖሚ አሻጥርን ለመከላከል በሚል ተግባራዊ ተድርጎ የነበረው በትይዩ እና በህጋዊ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ ያለው ልዩነት መስፋቱን ተከትሎ እንደሆነ አይዘነጋም።