ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የግንባር እንቄስቀሴዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን ሆን ብለውም ሆነ ባለማወቅ የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግሥት ጠየቀ፡፡
የግንባር ውሎ መረጃዎችን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዕዝ ከተፈቀደለት አካል ውጭ ማሰራጨትን በተመለከተ ባለፈው ሳምንት ክልከላ መውጣቱ ይታወሳል፡፡
ሆኖም መንግሥት አሁንም የግንባር መረጃዎችን በተመለከተ በየማኅበራዊ ትስስር ገፆች እያሰራጩ የሚገኙ አካላት መኖራቸውን አሳውቋል፡፡
የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ አገርን ማክበር የሚለው ሀሳብ የሚጀምረው የአገሪቱን ሕጎች በማክበር በመሆኑ አውቀውም ሆነ ሳያወቁ ይህን ሕግ እየተላለፉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ፍቃድ የሌላቸው ጋዜጠኞችን ማስጠንቀቂያ የሰጠው የመገናኛ ብዙኃን ባለስለጣን ከአዲስ አበባ የአልጄዚራ ሪፖርተር በመሆን የተለያዩ ዘገባዎችን ለረጅም ጊዜ ሲያቀርብ የነበረው ጋዜጠኛ ሳሙኤል ጌታቸው በኢትዮጵያ ፈቃድ የሌለው መሆኑን በትዊተር ገጹ ባወጣው መገለጫ አረጋግጧል።