ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ለሴኔጋል፣ ዚምባብዌ፣ ካሜሩን እና ኮቲዲቯር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጡ።
በወቅቱም በወቅታዊ አጋራዊ ሁኔታ፣ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ እንዲሁም በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይን አንስተው ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
ከሴኔጋሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ባደረጉት ውይይት ሴኔጋል የአፍሪካ ቻይና የትብብር የሚኒስትሮች ፎረምን በማስተናገዷ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ለአገሪቷ ዕድገት ብሎም ለአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትሥሥር እውን መሆን ትልቅ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል፡፡
በማብራሪያቸው በኢትዮ- ሱዳን ድንበር የተከሰተውን ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ በበኩላቸው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ወቅቱ የአፍሪካ ሀገራት በበርካታ አውዶች በአንድነት መንፈስ እና በትብብር ቆመው ማየት የምንፈልግበትም ነው ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።