በህወሃት ጄሌዎች የወደሙ ከተሞች ግንባታ ተጀመረ፤ በአፋር 57 የጤና ተቋማት ወድመዋል

በህወሃት ጄሌዎች የወደሙ ከተሞች ግንባታ ተጀመረ፤ በአፋር 57 የጤና ተቋማት ወድመዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የህወሃት ታጣቂዎች በጀግናው የመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም በፋኖና ሚሊሻ ተመቶ የለቀቃቸው ከተሞችን በማፈራረስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጽሙ ተገለጸ።

አሸባሪው እና ወራሪው የሕወሓት ቡድን ባደረሰው ጥቃት የወደሙ ንረቶችንና ተቋማትን የመገንባት ሰራ በፍጥነት መጀመራቸው የተገለጸ ሲሆን ኤሌክትሪክ ተቋርጦባቸው የቆዩ ከተሞችን መልሶ ለማገኛኘት እየተደረገ ባለው ከፍተኛ ርብርብ በትላንትናው ዕለት ነፃ መሆኑ የተገለፀው የሸዋሮቢት ከተማ ሙሉ ለሙሉ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አግኝቷል፡፡

በተጨማሪም በደብረ ሲና አካባቢ ያሉ አርማንያ፣ አስፋቸውና ጭራ ሜዳ የተባሉ የገጠር ከተሞች በዛሬው ዕለት የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ የተደረገ መሆኑን የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሙሉጌታ ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም የደብረ ሲናና ሌሎች ኤሌክትሪክ የተቋረጠባቸው ከተሞችን ኃይል ለማገኛኘት እየተሰራ እንደሆነ መግለጹን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ አመላክቷል፡፡

ከተሞቹን መልሶ የመገንባት ሂደት በ አፋጣኝ መጀመሩን ያመሰገኑት የሸዋሮቢትና የደረሲና አካባቢ ነዋሪዎች። እንኳን መከላከያና ልዩ ሀይላችን ደረሰልን እንጂ በህወሃት ጄሌዎች የወደመውን ከተማችንንና ንብረታችንን በፍጥነት እንተካዋለን ሲሉ ተደምጠዋል።

በተያያዘ በአፋር ክልል በተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽም የቆየው አጥፊው የህወሃት ቡድን በክልሉ በርካታ ንብረቶችንና ተቋማትን ያፈራረሰ ሲሆን 57 የጤና ተቋማትን ማወደሙን የክልሉ መንግስት ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY