ኢትዮጵያ ነገ ዜና || እየተከናወነ ለሚገኘው ሀገራዊ የህልውና ዘመቻ ያግዛል በሚል ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ የ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ የትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል።
ትምህርት ቤቶቹ ዝግ በሚሆኑበት ወቅት የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል መሰብሰብና የመርዳት ዘመቻዎች በስፋት እደሚካሄዱ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር፣ የክልልና የከተማ መስተዳደሮች የትምህርት ቢሮ አመራሮች ያደረጉትን ምክክር ተከትሎ ነው ውሳኔው የተላለፈው። በዉሳኔው መሰረት ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው የሚቆዩባቸዉን ቀናት የሚቋረጠውን ትምህርት ከግምት ውስጥ በማስገባት የትምህርት ተቋማቱ በሚያወጧቸው መርሃ ግብሮች መሰረት የማካካሻ ትምህርት የሚሰጥ ይሆናል።
በተጨማሪም የትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ ለሀገራዊ ዘመቻው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።