ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስቴር የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ገለጹ፡፡
ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ በጭፍራ ግምባር ተገኝተው ለሰራዊት አባላት ንግግር አድርገዋል።
ባደረጉት ንግግርም የሰራዊት አባላቱ ጀግኖች እንደሆኑ በመግለፅ፥ “የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው” ብለዋል።
የውስጥ ሀይሎች ለውጪ ወኪል ሆነው ኢትዮጵያን በሚወጉበት ወቅት በአንድነት ተነስተን አሸባሪዎችን ድባቅ እንመታለን ሲሉ አስገንዝበዋል ።
ይህ ትውልድ በዚህ ታሪካዊ ወቅት አሸባሪውን የመቅበር እድል በማግኘቱ ሊደሰት ይገባል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም ጄነራል ባጫ ዛሬ ቀይ መስመር በተባለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በመቅረብ በተለይ ሕወሃት በአማራ ክልል ነዋሪዎች ላይ ያደረሰውን ዘግናኝ ስራዎችና ሰብዓዊ ጥሰቶች የገለጹ ሲሆን የትሕነግ ሃይል ከአማራ ክልል ተባሮ ሲወጣ የዘረፈውን ማናቸውንም ነገር ይዞ እንዳይወጣ ህዝቡ በየቀበሌው እየወጣ በድንጋይ አስፓልት መንገዶችን እንዲዘጋ አሳሰዋል።