ትሕነግ በአፆኪያ ገመዛ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ተገለፀ

ትሕነግ በአፆኪያ ገመዛ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና አሸባሪው ትሕነግ በሰሜን ሸዋ ዞን አፆኪያ ገመዛ ወረዳ አንቦ ውሀ ቀበሌ ላይ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ተገለፀ።

እስካሁን ባለው መረጃ 70 የሚደርሱ ንፁሀን ከአምስት ዓመት ህፃን ጀምሮ አዛውንቶችና የአዕምሮ ታማሚ ሳይቀር የጅምላ ግድያው ሰለባ ሆነዋል።

የጅምላ ግድያው የተፈፀመው ኅዳር 24 ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጅዎች ዛሬም እየሞቱ መሆኑን ተገልጿል።

በአንድ መቃብር ላይ ብቻ እስከ 51 የሚደርሱ የጅምላ ግድያ ሰለባዎች እንደተቀበሩ የቀበሌዋ ነዋሪ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ምክንያቱ ደግሞ ወደ ህክምና ለመውሰድ አካባቢው በሽብር ቡድኑ ከበባ ውስጥ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የሟቾች ቁጥር እስከ 100 ሊደርስ እንደሚችል የጉዳቱ ሰለባ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

የጅምላ ግድያውን የፈፀመው የሽብር ቡድኑ ተረፈ ጁንታ በማህል ሜዳ እና ማጀቴ አካባቢ ድባቅ ተመቶ በሰሜን ሽዋ አፆኪያ ገመዛ ወረዳ አንቦ ውሀ ባለ ጫካ ለማለፍ ሲሞክር የአካባቢው ሚሊሻ አላሳልፍ ብሎ ስለገታውና ሙትና ቁስለኛ በማድረጉ ከመደምሰስ የተረፈው የሽብር ቡድኑ ቅሬት በአንቦ ውሃ ቀበሌ ንፁሃን ላይ የበቀል በትሩን አሳርፏል።

LEAVE A REPLY