ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሸባሪው ህወሃት በፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ማዕቀብ እንዲጣልበት ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ ተጻፈ፡፡
አሸባሪው ህወሃት በፈጸመውና እየፈጸመ ለሚገኘው ከባድ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ማዕቀብ እንዲጣልበት ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ ተጻፈ።
አሜሪካ በሽብር ቡድኑ ላይ በአስቸኳይ ማዕቀቡን ተግባራዊ እንድታደርግ የጠየቀው በአሜሪካ የኢትዮጵያዊያን ፐብሊክ ጉዳዮች ኮሚቴ ነው።
ኮሚቴው ጥያቄውን ያቀረበው ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ይፋዊ ደብዳቤ በመጻፍ ነው፡፡
ኮሚቴው ለሚኒስቴሩ ደብዳቤውን ለማጻፍም የተገደደው ህወሓት በፈጸመውና እየፈጸመ በሚገኝ ከባድ ኢ- ሰባአዊ ድርጊት ምክንያት መሆኑን ገልጿል፡፡
ኮሜቴው በደብዳቤው “በአሸባሪው ህወሓት ላይ በአሜሪካ መንግስት ሊጣሉ የታሰቡት ማዕቀቦች በአፋጣኝ እንዲተገበሩ በአክብሮት እንጠይቃለን” ብሏል፡፡
በግልጽ እንደሚታወቀው ብዙ የአሸባሪው ህወሓት አመራር አባላት ከፍተኛ ሃብትና ካፒታል በውጭ አገር አላቸው ያለው ኮሚቴው ሆኖም አሜሪካም ሆኑ ሌሎች የአለም ማህበረሰብ አባላት በአሸባሪው ህወሓት አባላት ላይ ያነጣጠረ ማዕቀብ አልተገበሩም ነው ያለው።
በእነዚህ ግለሰቦች እና ድርጅቱ ላይ ማዕቀብ መጣል፤ በኢትዮጵያ የሽብር ድርጊትን በመከላከል ንጹሃንን ከአሰቃቂ ጥቃት መታደግ ይቻላል ሲል አስረድተዋል።