ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ታሪካዊቷ የደሴ ከተማና የንግድና የኢንዱስትሪ ኮሪደር የሆነችው ኮምቦልቻ ከተማ፣ በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጥተዋል ሲል የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አሳውቋል።
ጀግናው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖና የአከባቢው ሚሊሻ በአንድ እዝ ባደረጉት የማጥቃት እርምጃ ነው ከተሞቹ ሙሉ በሙሉ ነጻ መወጣታቸው የተገለጸው።
ከተሞቹ ነጻ የወጡት ከቀናት በፊት ቢሆንም የቤት ለቤት የማጽዳት ሂደቶች ተከናውነው እስኪጠናቀቁ ይፋ ሳይደረግ መዘግየቱን የነገ ምንጮች ገለፀዋል።
የህወሀት ታጣቂዎች ከተሞቹ ውስጥ ተሰግስገው በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዳይፈጽሙ የደሴና የኮምበልቻ ተወለጅ ፋኖና ሚሊሻዎች ቀደመው በመግባት የማፅዳቱ ሰራ ላይ ከፍተኛ አሰተዋፆ እንዳደረጉ ለመረዳት ችለናል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ከደሴና ኮምቦልቻ በተጨማሪ በምሥራቅ ግንባር ባቲን ቀርሳን ገርባንና ደጋንን ነጻ ያወጣ ሲሆን በሐርቡ ግንባር ደግሞ ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።