የተዘረፉ የሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ንብረቶች እየተመለሱ መሆኑ ተገለፀ

የተዘረፉ የሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት ንብረቶች እየተመለሱ መሆኑ ተገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአሸባሪው የሕወሓት ወራሪ ቡድን ምክንያት ተዘርፎና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ተከፋፍለው የነበሩ የሸዋሮቢት ማረሚያ ማዕከል ሃብት ንብረቶች እየተመለሱ ነው፡፡

ቀሪ ንብረቶችም በፍጥነት መመለስ እንዲችሉ የአካባቢው ማኅበረስብ ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባባር እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል፡፡

አሸባሪው ቡድን የሸዋሮቢት ከተማን ተቆጣጥሮ በቆየባቸው ጥቂት ቀናት በከተማዋ የሚገኙ የመንግሥትና የግለሰብ ተቋማትን ሃብትና ንብረት በሚችለው ልክ ዘርፎ መውሰዱን የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አሳውቋል፡፡

ዘረፋና ውድመት ከተፈፀመባቸው የመንግሥት ተቋማት መካከል በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ስር የሚተዳደረው የሸዋሮበት ማረሚያ ማዕከል መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል፡፡

LEAVE A REPLY