ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሰብአዊ መብት ጥበቃ ስም በውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረግን ሙከራ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ አስታወቁ።
ዶክተር ጌዲዮን መቀመጫቸውን በጄኔቫ ላደረጉ የአፍሪካ አምባሳደሮች ቡድን በኢትዮጵያ ስላለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም በኢትዮጵያ ስላለው ሰብዓዊ መብት ጉዳይ አስመልክቶ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የሚስተጋቡት ውንጀላዎች እና አደገኛ ንግግሮችን ምንም አይነት እውነትነት የሌላቸውን የሰብዓዊ መብትን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ ለመጠቀም የሚፈልጉ አገራት የሚያሰራጩት መሰረተ ቢስ ውንጃላ ናቸው።
በዚህም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥበቃን ሽፋን በማድረግ በውስጥ ጉዳይ ለመግባት የሚደረግ ሙከራን ኢትዮጵያ አትቀበልም ብለዋል።
እንደዚህ አይነት ጣልቃ ገብነት የሰብዓዊ መብት አጀንዳዎችን ለማራመድ የሚደረገውን እውነተኛ ጥረት የሚጎዳ መሆኑንም ጠቁመዋል።