ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠ/ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት፤ የመጀመሪያውን ምእራፍ አጠናቀው ለተወሰኑ ጊዜያት ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ገልፀዋል።
” ዛሬም ሆነ ወደፊት ጠላቶቻችን ጉልበታቸው ዝሎ የጥላቻና የጠበኝነትን መንገድ ጥለው የፍቅር እና የሰላምን መንገድ እስኪመርጡ ትግላችን ይቀጥላል ” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረብኩትን ጥሪ ተቀብላችሁ ህይወታችሁን ጉልበታችሁን ሀብታችሁን ፣ እውቀታችሁን ጊዜያችሁንና ሞያችሁን ለሰጣችሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ “lሲሉ ገልፀዋል።