ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አፍሪካ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እንደሚታገሉ አሳወቁ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አፍሪካ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት እንደሚታገሉ አሳወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ከሌሎች የአፍሪካ አገራት መሪዎች ጋር እንደሚታገሉ አሳወቁ፡፡

1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ሕዝብ ያላት አኅጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ነው በቲውተር ገጻቸው አሳውቀዋል፡፡

በአኅጉሪቱ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ ምክክር ያለአኅጉሪቱ ተወካይ እየተካሄደ የሚቀጥልበት አግባብ መቆም እንዳለበትም አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳህል እና የደቡብ አፍሪካ አቻቸው ሲሪል ራማፎሳ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ድጋፍ እያገኙ ነው፡፡

ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች ትናንት በጋራ በሰጡት መግለጫ የፀጥታው ምክር ቤት ሚዛናዊ ያልሆነ የቋሚ ተወካይ ስብጥር መያዙን በመጥቀስ ከዚህ በኋላ ይህ ሊቀጥል አይገባም ብለዋል፡፡ አንድም የአፍሪካ አገር ቋሚ መቀመጫ የሌለው መሆኑ ተቀባይነት እንደሌለው አቋማቸውን አሳውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY