ኩባ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የተቀናጀ ጫና እንደምታወግዝ አአስታወቀች

ኩባ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የተቀናጀ ጫና እንደምታወግዝ አአስታወቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙት የኩባ አምባሳደር ጆርግ ኤፍ.ኤል ኒኮላስ አንዳንድ አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያካሂዱትን የተቀናጀ ጫና እና ሃሰተኛ የሚድያ ዘመቻ የኩባ መንግስት እንደሚያወግዘው ገለጹ።

አምባሳደሩ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኘሮቶኮል ጉዳዮች ምክትል ሹም አምባሳደር አለማየሁ ሰዋአገኝ አቅርበዋል።

በወቅቱም አምባሳደሩ፥ ኩባ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት አንዳንድ አገራት በኢትዮጵያ ላይ የተቀናጀ ጫና እና የሃሰተኛ የሚድያ ዘመቻ እያካሄዱባት እንደሚገኝ በማንሳት የኩባ መንግስት ይህን ድርጊት እንደሚያወግዝ ነው የገለጹት።

እንደቀድሞ ሁሉ ኩባ ከኢትዮጵያ ጎን መሆኗን የገለፁ ሲሆን ÷ አስፈላጊውን ዲኘሎማሲያዊ ድጋፍ እንደምትሰጥ አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ጆርግ ኤፍ ኤል ኒኮላስ በሥራ ቆይታቸው በትምህርት፣ ህክምና እና የስኳር ልማት መስክ ያለውን የሁለቱን አገራት ትበብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል። አምባሳደር አለማየሁ በበኩላቸው÷ ኩባውያን ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት መከበር ታላቅ መስዕዋትነት መክፈላቸውን በማስታወስ የግንኙነታቸውን ጥንካሬ ገልፀዋል።

አገራቱ ህዝቦቻቸውን ይበልጥ ተጠቃሚ በሚያደርጉ ዘርፎች ላይ አተኩረው ግንኙነታቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸውም ማንሳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል

LEAVE A REPLY