ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ዶ/ር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም ሆነ የአፍሪካ ህብረት መስራች አባል እንደ መሆኗ መጠን፣ የሀገራዊ ሉዓላዊነት ክብርን መሰረት ያደረገ የባለብዙ ወገን ግንኙነት አራማጅ ነች ብለዋል።
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይም ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ ከአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እና የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል ጋር ውጤታማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።