ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኮምቦልቻ የሚገኘው የደረቅ ወደብ ተርሚናል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሕወሓት መዉደሙን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
የሕወሓት ኃይሎች በደረቅ ወደብ ተርሚናሉ ላይ ባደረሱት ውድመትና ዘረፋ ከ251 በላይ ደንበኞች ንብረቶችን የያዙ ኮንቴይነሮች መዘረፋቸውን አዲስ ዘይቤ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ኮምኒኬሽን ቢሮ ማረጋገጥ ችላለች።
በኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ንብረት የነበራቸውን ግለሰቦች ድርጅቱ እንደሚያነጋግራቸው የተገለጸ ሲሆን በወደቡ የጉዳት መጠን ዙሪያ ዝርዝር መረጃ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።