ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የተራራ ኔትዎርክ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ከመኖሪያ ቤቱ በፖሊሶች መወሰዱን ተራራ ኔትዎርክ ገለጸ።
ጋዜጠኛ ታምራት ከመኖሪያ ቤቱ የተወሰደው ከጠዋቱ 4:30 ገደማ ነው የተባለ ሲሆን ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ተወስዷል።
ታምራት የሚሰራበት መስሪያ ቤት እንደገለጸው የጋዜጠኛውን የመኖሪያ ቤት እና ቢሮ የፈተሹት ፖሊሶች ለመረጃ ይፈለጋሉ ያሏቸውን የሚዲያ ቁሶች ማለትም ላፕቶፕ፣ ኮምፒዩተሮች፣ መቅረጸ ድምጽ፣ ፍላሽ ሚሞሪ እና ሌሎች የስራ መገልገያዎች በሙሉ ተወስደዋል።
ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከሚታወቁ ሀገራት ውሰጥ የተመደበች ሲሆን በተለይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተወጀ ጀመሮ በርካታ ጋዜጠኞች ማሰሯን ሲፒጄ የተባለው የጋዜጠኞች ተሟጋች ድርጀት ይፋ አድርጓል።