ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ታኅሣሥ 2/2014 (ዋልታ) የአማራ ባለሃብቶች ጥምረት ለአገሩ ኅልውና ከልጁ ጋር በክብር ለተሰዋው አቶ እሸቴ ሞገስ ቤተሰቦች 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
የተደረገውን ድጋፍ የባለሃብቶቹ ጥምረት ተወካይ አቶ ዮናስ መኮንን ለአቶ እሸቴ ሞገስ ታናሽ ወንድም ዶክተር ይተብቱ ሞገስ አበርክተዋል።
አቶ እሸቴ ሞገስ ከልጃቸው ይታገስ እሸቴ ጋር በመሆን በሸዋሮቢት ሳላይሽ ላይ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን የአሸባሪው ሕወሓት ዘጠኝ ወራሪ ኃይሎችን በጀግንነት በመግደል በክብር መሰዋታቸው ይታወሳል።