ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ህወሓት የፈፀማቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መመልከት እንዲችሉ መንግስት እየሰራሁ...

ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ህወሓት የፈፀማቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መመልከት እንዲችሉ መንግስት እየሰራሁ ነዉ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሸባሪው ህወሓት የፈጸማቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ያደረሳቸውን ቁሳዊ ውድመቶች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ እየተሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም መንግስት የሽብር ቡድኑ በወረራ ይዟቸው በነበሩ የአፋር እና አማራ ክልሎች የፈጸማቸውን ለማመን የሚከብዱ ዘግናኝ ግፎች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ እየሰራ መሆኑን ልጸዋል፡፡

አክለውም መንግስት ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት የፈፀማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ያደረሳቸውን ቁሳዊ ውድመቶች በአካል ተገኝተው እዲመለከቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ትናንት በተከበረው የአለም የሰብዓዊ መብት ቀን በሽብር ቡድኑ ጥቃት የተፈፀመባቸው ዜጎች ታስበው መዋላቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ለዚህም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተቋቋመ ግብረ ሃይል መኖሩን ነው ያመለከቱት።

የግብረ ሃይሉ ዋና አላማም የሽብር ቡድኑ የፈፀማቸውን ሙሉ የወንጀል ምርመራዎች በማጠናቀቅ አጥፊዎቹ ላይ ክስ መመስረት እና በሽብር ቡድኑ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም የሚደረገውን የሀብት ማሰባሰብ ሰራ መምራት ይሆናል ብለዋል ሚኒስትር ዴታአዋ፡

LEAVE A REPLY