ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መዓዛ መሀመድ ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ በሚል ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠዋት ከመኖሪያ ቤቷ ተወስዳለች።
አባይ ሚድያ ላይ በመስራት በርካታ ዘገባዎችን በመዘገብ የምትታወቀው ጋዜጠኛ መአዛ በቅርቡ ከከፈተችው ሮሃ ቲቪ በተጨማሪ በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ ሃሳቧን በነጻነት በማጋራት ትታወቃለች።
ጋዜጠኛዋ የተወሰደችበትን የፖሊስ ጣቢያ እስካሁን ማወቅ አልቻለችም። የኢትዮጵያ መንግስት ተላንትና ጋዜጠኛ ታምራት ነገራን ማሰሩ የተዘገበ ሲሆን አለማቀፍ የጋዜጠኛ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተመልክቷል።
ጋዜጠኞች ሃሳባሃቸውን ለመግለጽ የሚያበሳጭ ንግ ግር በተናገሩ ቁጥር ወጣት ሽማግሌውን መቀፍደድ ተገቢ አይደለም። ያለው በካናዳ የህግ ባለሙያ ጠበቃ ተክለሚካኤል አበበ አስቸኳይ ግዜ አዋጅ የሚመዘዘው አንድን ነገር በተለመደው ሕግ ማስከበር ስርአት መቋቋም ካልተቻለ ነው። እነዚሕ ልጆች ላይ አዋጁን መምዘዝ አያስፈልግም ነበር። አስሮ መሰወር ንቀት ነው። ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።