ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል መርህ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖቸ የሚደረስ የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት ቀጥሏል።
በዚህም መሰረት በቫንኩቨር ካናዳ የሚኖሩ ትወልደ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ቅዳሜ ታህሳሥ 2 ቀን 2014 ዓም ባደረጉት የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጀት ላይ 90 ሺህ የሚጠጋ የካናዳ ዶላር መሰብሰባቸው ተመልክቷል።
በዝግጅቱ ላይ ካናዳ አርት ባትል በመባል የሚታወቀው ሀገር አቀፍ የሰአሊዎች የውድድር መድረክ ላይ በተከታታይ በማሸነፍ የሚታወቀው የአርቲስት ያሬድ ንጉሡ ሊሚትድ ኮፒ የአርት ስራ ለጨረታ ቀረቦ 7ሺህ ዶላር ተሽጧል።
በርከታ ኢትዮጵያውያንና እንግዶች በተገኙበት በዚሁ የዕርዳታ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ የ8 አመት ታዳጊ ናፍቆት አትክልት በፒጊ ባንክ ያጠራቀመውን ሳንቲም 381 ዶላር በጦርነቱ ለተጎዱ ሕጻናት እንዲደርስ አበርክቷል።No በካናዳና አሜሪካ የሚኖሩ ህፃናትም በጦርነቱ ለተገዱ ሕፃናት በተመሳሳይ እንዲረዱ መልእክቱን አስተላልፏል።
በጨረታው በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት የተሰሩ ፎጣዎች እስከ 4500 ዶላር የተሸጡ ሲሆን በድምሩ 90ሺህ ዶለር የሚጠጋ ገንዘብ መሰበሰቡን ለመረዳት ችለናል።
ECNAS (ኢክናስ) በመባል በሚታወቀው ካናዳ አቀፍ ተቋም ባዘጋጀው የእርዳታ ማሰባሰብ መርሀግብር ላይ ከቪክቶሪያ እና አጎራባች ከተሞች የመጡ ወገኖችም ተሣትፈዋል።