የሕወሓት ቡድን ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች ባጠረ ጊዜ ለማስተካከል እየተሰራ ነዉ ተባለ

የሕወሓት ቡድን ያወደማቸውን መሰረተ ልማቶች ባጠረ ጊዜ ለማስተካከል እየተሰራ ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አሸባሪው ትህነግ ያወደማቸውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች በማስተካከል ባጠረ ጊዜ ሕብረተሰቡ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የትራንስፎርሜሽንና ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ሀብታሙ ውቤ አሸባሪው በወረራቸው የአማራና አፋር ክልል ሕብረተሰቡ የሚገለገልባቸውን ማኅ በራዊ ተቋማትና መሰረተ ልማቶችን ማውደሙን አስታውሰዋል።

ከእነዚህ ውስጥም የኤሌክትሪክ መስመሮችና ታወሮች ላይ ያደረሰው ውድመት የሚጠቀስ ነው ያሉት የሥራ ኃላፊው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ባጠረ ጊዜ ሕብረተሰቡ አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡

LEAVE A REPLY