ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ጋር መወያየታቸውን ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከቱርክ ፕሬዚዳንት ረጅብ ጠይብ ኤርዶኻን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ከቱርክና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ እኔና የልዑካን ቡድኔ ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።

የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ሁሌም በመከባበር ላይ የተመሠረተ ነው። ትብብራችን በገንቢ ተሳትፎ ላይ በመመሥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሦስተኛው የቱርክ አፍሪካ አጋርነት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ቱርክ ማቅናታቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY