ተመድ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ አነሳ

ተመድ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ አነሳ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ወሳኝ ያልሆኑ የውጭ ጉዞዎች ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሣቱን አስታውቋል።

እገዳው የተነሣው በአሁኑ ሰዓት በአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ የፀጥታው ሁኔታ ጉልህ መሻሻል በማሳየቱ እንደሆነ በተመድ የደህንነት እና የፀጥታ ጉዳዮች ኃላፊ ጊልስ ሚሾ ገልጸዋል።

ይህን ጉዳይ እንዲከታተል ኃላፊነት የተሰጠው አካል ከፀጥታ አስተዳደር ቡድን ጋር ባደረገው ምክክር በተጠቀሱት አካባቢዎች ጉልህ መሻሻል በመታየቱ እገዳው በአስቸኳይ እንዲነሣ ምክረ-ሐሳብ ማቅርቡ ተገልጿል።

በመሆኑም ኃላፊነት የተሰጠው አካል ያቀረበው ምክረ-ሐሳብ በአፋጣኝ ተግባራዊ እንዲሆን እና ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ወሳኝ ያልሆኑ የውጭ ጉዞዎች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ በአስቸኳይ እንዲነሣ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የተመድ የደህንነት እና የፀጥታ ዲፓርትመንት ኃላፊው ጊልስ ሚሾ አስታውቀዋል።

LEAVE A REPLY