ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የሽብር ቡድኑ ነሐሴ 3/2013 መርሳ ከተማ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 8 ድረስ የከተማዋን ንብረት መዝረፉን እና ወጣቶችን መረሸኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ቤት እየተፈተሸ ሽሮና በርበሬ ሳይቀር ተወስዷል የሚሉት ነዋሪዎች ሴቶችና ህፃናት ተደፍረዋል፣ የመንግሥት ተቋማት ተዘርፈዋል አለፍ ሲልም እንዲወድሙ ተደርገዋል ብለዋል።
የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ ጥምር ጦር ባደረገው ተጋድሎ ከአሸባሪው ትሕነግ ከተማዋ ነፃ በመውጣቷ ሕዝቡም ነፃ መውጣቱን ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት።