ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ከእዚህ ቀደም በሽብር ወንጀል ተከሳ በነጻ ተሰናብታ የነበርችው ተከሳሽ ላምሮት ከማል የ3 ወራት እስር እንድትቀጣ ብያኔ ሰጥቷል።
ይሁንና ተከሳሿ በቁጥጥር ስር ከዋለችበት ከሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ 3 ወራት በፖሊስ ጣቢያ እንዲሁም 1 አመት ከ5 ወራት ደግሞ በማረሚያ ቤት በዕስር መቆየቷን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በነጻ አሰናብቷቷል።
ላምሮት ከማል በሽብር ወንጀል በተከሰሰችበት ወቅት በቂ ማስረጃ ባለመቅረቡ በነጻ ከተሰናበተች በኋላ የዓቃቤ ህግን ይግባኝ ተከትሎ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ በሽጉጥ በተመታበት ጊዜ በቸልተኝነት እርዳታ ባለመስጠት በወንጀል ህግ አንቀጽ 575 ንዑስ ቁ 1 እንድትከላከል ትዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።
ተከሳሿ በቀረበባት ወንጀል ላይ መከላከያ ማስረጃ የለኝም ማለቷን ተከትሎ በትላንትናው እለት የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶባት ለቅጣት ብያኔ ዛሬ ታህሳስ 15 2014 ዓ.ም. ቀጠሮ በተሰጠበት መሰረት ፍርድ ቤቱ የ3 ወራት እስር በይኖባታል።
ተከሳሿም በፍርድ ሂደቷ በእስር ላይ ከ3 ወራት በላይ መቆየቷን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በነጻ ሊያሰናብታት ችለዋል።