ውሳኔዎቻችን ስሜታዊ ሳይሆኑ ዘላቂ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለፁ

ውሳኔዎቻችን ስሜታዊ ሳይሆኑ ዘላቂ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከእንግዲህ አሸባሪው ኃይል በቃዠ ቁጥር የፈለገውን የሚያደርግበት ሁኔታ የለም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ የለም ስንል አይፈልግም ወይም አይሞክርም ማለታችን አይደለም።

አንድነታችን ጠብቀን እስከቆምን ድረስ መቼም ቢሆን ኢትዮጵያ አትሸነፍም፡፡ የኢትዮጵያ ድል መሠረቱ የጠላት ድክመት ሳይሆን የእኛ ብርታትና ትብብር መሆኑን አውቀን፣ ይበልጥ አንድነታችንን አጠንክረን መቆም ይገባናል፡፡

የትግራይ እናቶች ይሄንን ሁሉ ምስቅልቅል ያመጣባቸውንና ልጆቻቸውን ነጥቆ ያስጨረሰባቸውን አሸባሪ ኃይል መጠየቅ አለባቸው ብለዋል

ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄንን አሸባሪ ከጫንቃው ላይ ያስወገደው በመራራ ትግሉ ነው የትግራይ ሕዝብም እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ይሄንን አሸባሪ ታግሎ የማስወገድ አቅምና ችሎታው አለው የሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ድጋፍና እርዳታ በአስፈለገ ጊዜም የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ከክልሉ ሕዝብ ጎን ይቆማል ብለዋል።

የማንኛውም ውሳኔያችን መርሕ ኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ድል እንድትጎናጸፍ ማስቻል ነው፤ ግዛታዊ አንድነታችን የሚጠበቅበትና በዘላቂነት ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆንበትን መንገድ መቀየስ ነው ብለዋል።

LEAVE A REPLY