ማራቶን ሞተርስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ አስመረቀ

ማራቶን ሞተርስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ አስመረቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ማራቶን ሞተርስ ኢንጂነሪንግ ፒኤልሲ የሀዩንዳይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ስቴሽን አስመረቀ።

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ እንደተናገረው ኢትዮጵያ ወደ ከፍታዋ እየሄደች ነው፤ ይህ ከፍታዋ ደግሞ በቴክኖሎጂ ጭምር እውን ይሆናል፡፡

እስከ ዛሬ በጦርነት ሰበር ዜናዎች ብንቆይም ከዚህ በኋላ ግን የቴክኖሎጂ ሰበር ዜናም በየሳምንቱ እንሰማለን ብሏል።

የነዳጅ ምርት የለንም፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ግን አለን፤ ይህንን ማሳደግ ይገባል ነው ያለው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ፡፡ ለኢትዮጵያችን ከፍታ እንቅፋት መሆን የለብንም፤ ከቻልን መተባበር ካልቻልን አርፈን መቀመጥ ይኖርብናል ብለዋል።

በምርቃቱ ላይ የድርጅቱ መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መልካሙ አሰፋ እንዳስታወቁት የኤሌክትሪክ ቻርጅ ስቴሽኖቹ በ15 ደቂቃ ሙሉ ቻርጅ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን
ተሽከርካሪዎቹም በአንድ ጊዜ ቻርጅ እስከ 300 ኪሎ ሜትር ድረስ መጓዝ ይችላሉ ተብሏል።
በምርቃቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

LEAVE A REPLY